አቡጊዳ መግብራት

ስለ እኛ

About Us

እኛ በሶፍትዌር ልማት ላይ የተሠማራን ሲሆን ለእርስዎ ፍላጎት ተስማሚ የሆኑ ጥራት ያላቸው መተግበሪያዎችንና ሶፈትዌሮችን እናቀርባለን። የሞባይል፣ የዴስክቶፕ እና የድር መተግበሪያዎች እያለማን የምንገኝ ሲሆን ለተለያዩ ሥርዓተ ሥሪቶች ማለትም ዊንዶውስ(Windows)፣ አንድሮይድ(Android) እና አይ ኦ ኤስ (iOS) ሁሉን አቀፍ እና ለአጠቃቀም ምቹ የሆኑ ሥራዎችን ይዘን ቀርበናል። ለኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ሽግግር ባለን ቁርጠኝነት መሠረት የሚከተሉትን እናዘጋጃለን፦
✔️ የዕለት ተዕለት ተግባራትንና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚረዱ ቀላል መተግበሪያዎች
✔️ የላቀ አገልግሎት የሚሰጡ በኢንተርፕራይዝ ደረጃ ያሉ መተግበሪያዎች
✔️ ኢትዮጵያዊ እሴት የጠበቁ የልጆችና አዋቂዎች መማሪያ መተግበሪያዎች በግእዝ፣ በአማርኛና ሌሎች ቋንቋዎች
በነፃ፣ በትንሽ ዋጋ እና ከሌሎች ጋር በመተባበር ወደ እናንተ እናደርሳለን።
መሪ ቃላችን ግልጽ ነው፦ “የኛን በእኛው ለእኛ!”
ሀገራዊ እሴታችንን ጠብቀን ለኢትዮጵያና ሌላው ማኅበረሰብ ሊጠቅም የሚችል ሥራ ለማቅረብ ቁርጠኞች ነን።

We are engaged in software development, providing high-quality applications and software tailored to your specific needs. We develop mobile, desktop, and web applications, offering comprehensive and user-friendly solutions for various operating systems, including Windows, Android, and iOS. As part of our commitment to Ethiopian technological advancement, we develop:
✔️ Simple applications to streamline daily tasks and enhance productivity.
✔️ Advanced, enterprise-level applications offering superior functionality.
✔️ Educational applications for children and adults, preserving Ethiopian values, in Ge'ez, Amharic, and other languages.
We make these solutions available to you for free, at a low cost, and through collaborations with others.
Our motto is clear: "Ours, By Us, For Us!"
We are committed to providing work that benefits Ethiopia and the broader community, all while preserving our national values.