Wednesday, January 8, 2025

ፕሮ ግእዝ ግቤትን ያውርዱ Download Pro Geez IME



ፕሮ ግእዝ

ፕሮ ግእዝ፦ ቀላልና ዘመናዊ የግቤት መርትዕ

ፓወር ግእዝ 2025

አብዛኞቻችን የምንጠቀመው የቅርብ ጊዜ ሶፍትዌሮችን እና መተግበሪያዎችን ነው። ነገር ግን እንደ ኦፊስ 2021 ያሉ የጽሕፈት መገልገያ ሶፍትዌሮች በአሮጌው ፓወር ግእዝ መተየቢያ አይሠሩም። ብዙ ሰው ሲጠቀምበት የነበረው ፓወር ግእዝ ከኦፊስ 2010 በኋላ መስራት አቁሟል። በተጨማሪም የፓወር ግእዝ ግቤት ለአጠቃቀም አስቸጋሪ የሆኑ አዝራሮችን ጥምረት ያቀፈ ነው። ለምሳሌ፣ "ቧ" የሚለውን ፊደል ለመተየብ አራት ቁልፎችን መጫን ያስፈልጋል ("B + CapsLock + W + A")። የማክሮሶፍት ዊንዶውስ ግቤትም ምቹ አለመሆኑ ብቻ  ሳይሆን  ያልተለመደ  በመሆኑ ብዙ ሰው ሲጠቀምበት ይቸገራል። አብዛኛው ሰው ኮምፒውተር ላይ መጻፍ የለመደው በፓወር ግእዝ ስለሆነ እንደ አዲስ ላለመማር ሲባል መሠረታዊ የቁልፍ ሰሌዳው ውቅር ፓወር ግእዝን እንዲመስል ተደርጓል። ነገር ግን እንደ ፓወር ግእዝ ባሉ የግቤት ሥርዓቶች ከነአካቴው ያልነበሩና ለመጻፍ አስቸጋሪ የነበሩ ድቃላ ፊደላት፣ በልዩ ልዩ ቋንቋዎች የሚገኙ ፊደላት፣ የግእዝ ቁጥሮችና የግእዝ ኅፁፃን ፊዳላት፣ ሥርዓተ ነጥቦች እና የዜማ ምልክቶች በዋናው የቁልፍ ሰሌዳ ለአጻጻፍ ቀላል በሆነ መንገድ ቀርበዋል። ከዚህ በኋላ እነዚህን ሁሉ ከምልክት ማኅደር ወይም ከሌሎች ጽሑፎች መቅዳት ሳይጠበቅብን በዋናው ቁልፍ ሰሌዳ በቀጥታ መጻፍ እንችላለን። ፕሮ ግእዝን ልዩ የሚያደርገው ይህ ነው።

ፕሮ ግእዝ የሚሰጣቸው የላቁ አገልግሎቶች

  • ለብዙ ቋንቋዎች የሚሆን፦ ግእዝ፣ ትግርኛ፣ ትግሬ፣ አማርኛ፣ ጉራጊኛ፣ አገውኛ፣ ኸምጠኛ፣ ሀረሪ፣ አርጎባ፣ ሲልጤ፣ ዛይ እና ሌሎችንም ተመሳሳይ ቋንቋዎች የፊደል ገበታ በዋናው የቁልፍ ሰሌዳ ላይ በማካተት ቀርቧል። ለምሳሌ፦ ካፕስሎክ (CapsLock) በማብራት "ጘ"፣ "ቐ" እና "ዸ" ያሉ ፊደሎችን ከምልክት ማኅደር ወይም ከሌሎች ጽሑፎች መገልበጥ ሳይጠበቅብዎ በቀጥታ መተየብ ይችላሉ።
  • የዜማ ምልክቶችን መያዙ፦ ፕሮ ግእዝ ግቤት የቅዱስ ያሬድን የዜማ ምልክቶች በዋናው ቁልፍ ሰሌዳ በማካተት የዜማ መጻፍትን ለማመልከት እንዲቻል አዲስ ግኝት ይዞ ቀርቧል።
  • ቀላል አጻጻፍ፦ በጥናት ላይ ተመርኩዞ የተዘጋጀው ፕሮ ግእዝ አነስተኛ የቁልፍ አዝራሮችን ጥምረት ይጠቀማል። ለምሳሌ፦ ሁለት ቁልፍ ብቻ ማለትም "b" + "aa" በመጫን "ቧ" ብለን መጻፍ እንችላለን። ይህም በፍጥነት እና በቀላሉ ለመፃፍ ያስችላል።
  • ሰፊ አገልግሎት፦ ለማይክሮሶፍት ኦፊስ ምርቶች ማለትም ወርድ፣ ኤክሴል… ብቻ ሳይሆን ኖትፓድ፣ ስቲኪ ኖትስ እና ሌሎችም የጽሑፍ መርትዓት እንዲሁም ዩቲዩብ፣ ቴሌግራም፣ ፌስቡክና የመሳሰሉት መግብራት ላይ በቀጥታ መጻፍ፣ መፈለግና መሰል አግልግሎቶችን ማግኘት ያስችላል።
  • ፋይል አያያዝን ምቹ ማድረግ፦ በሀገርኛ ቋንቋችን ፋይሎችና ማቀፊያዎችን በቀጥታ መፈለግ፣ መሰየምና ስም ማስተካከል እንችላለን።
  • የድር ፍለጋ ተደራሽነት፦ ድር ማሰሻዎችን (Web Browsers) ወይም የድር መግብራትን ተጠቅመን መረጃ መፈለግ ስንሻ ሌላ ቦታ ጽፈን መገልበጥ ሳይጠበቅብን በሀገርኛ ቋንቋችን በቀጥታ በመጻፍ መፈለግ እንችላለን።
  • ለሶፍትዌር አበልጻጊዎች ምቹ፦ ለሶፍትዌር አበልጻጊዎች መተግበሪያዎችን በሀገርኛ ቋንቋ ማበልጸግ ስንፈልግ አስፈላጊ ጽሑፍ ሌላ ቦታ ጽፈን መቅዳትና መገልበጥ ሳይጠበቅብን በቀጥታ IDE ላይ መጻፍ ያስችለናል።
  • ለሁሉም ዊንዶውስ ተስማሚነት፦ ፕሮ ግእዝ ከዊንዶውስ 7 እስከ አሁኑ ዊንዶውስ 11 ሥሪት ተስማሚ ነው።

የአጫጫን መመሪያ

መተግበሪያው አዲስ ስለሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲጭኑት የሚከተሉት ሁለት ነገሮች ሊያጋጥምዎት ይችላል።

1ኛ ስማርት ስክሪን (ኢንተርኔት ጋር ከተገናኙ)

ይህ በማንኛውም አዲስ ሶፍትዌር የተለመደ ስለሆነ የሚከተለውን መመሪያ በመከተል ይጫኑት። 




2ኛ. ዊንዶውስ ዲፌንደር

ዊንዶውስ ዲፌንደር አዳዲስ ሶፍትዌሮችን እስኪላመድ ድረስ እንደ ባዳ ስለሚቆጥራቸው ሲጭኑ ሊያጠፋብዎ ይችላል። እንዲህ ዓይነት ነገር ከገጠመዎ ዊንዶውስ ዲፌንደርን ቅድሚያ በመዝጋት መጫን ይችላሉ፤ ከዚያ ድፌንደርዎን ማብራት ነው።



Pro Geez IME

Pro Geez: Simplified and Modernized Input Editor

Power Geez 2025

Most of us use the latest software and applications. However, word processing software like Office 2021 doesn't work with the old Power Geez input method. Power Geez, widely used in the past, stopped working after Office 2010. Moreover, Power Ge’ez is very difficult to use, requiring complex key combinations. For example, typing the letter "" requires four key presses ("B + CapsLock + W + A").  Even the default Windows Default IME, Microsoft Windows Input Method is also inconvenient and unusual, making it difficult for many users. Since most people are familiarized to typing on a computer using Power Geez, the basic keyboard layout has been designed to resemble it to avoid the need for re-learning new key combination. However, Pro Ge'ez introduces features that go beyond Power Ge'ez’s and other IMEs capabilities, making it easier to type previously hard-to-access symbols, complex and unique characters, letters specific to various languages, rare Ge'ez letters, Ge'ez numerals, punctuation marks, and other symbols are now directly available on the main keyboard layout in an easy-to-use way for typing.  This is what makes Proto-Ge'ez IME unique.

Advanced Features of Pro Geez

  • Multi-lingual Support: Pro Geez incorporates the alphabets of numerous languages including Ge'ez, Tigrinya, Tigre, Amharic, Gurage, Agaw, Kemant, Harari, Argobba, Silt'e, Zay, and etc, directly on the main keyboard. For example, by turning on Caps Lock (CapsLock), you can directly type letters like "," "," and "" without having to search for them in a symbol library or copy them from other sources.
  • Incorporation of Tonal Marks: Pro Geez input incorporates St. Yared's tonal marks directly onto the main keyboard, representing a significant advancement in music notation.
  • Simplified Typing: Since Pro Ge’ez was developed based on research, it utilizes minimal key combinations for fast typing. For example, Pro Geez allows typing "" with only two keys: "b" + "aa". This enables faster and easier typing.
  • Wide Compatibility: Pro Ge’ez is not only just for Microsoft Office products (Word, Excel, etc.), but also it works seamlessly with various text editors, including Notepad, Sticky Notes, and also different software and applications like YouTube, Telegram, Facebook etc., allowing for direct typing, searching, and other functionalities.
  • Improved File Management: Allows direct searching, naming, and renaming of files and folders in Ge’ez based local languages.
  • Web Search Accessibility: When searching for information using web browsers, or web apps you can type and search directly in your native language without copying what you want from elsewhere.
  • Developer-Friendly: For software developers, it allows direct typing in the IDE (Integrated Development Environment) when enriching applications with native language text, eliminating the need to copy and paste from other sources.
  • Windows Compatibility: Pro Geez is compatible with Windows versions from Windows 7 to the current Windows 11.

Installation Guide

Because the software is newly published, you might experience these two things when installing it for the first time:

1.     Smart Screen (If connected to the Internet):

  This is common with any new software, so follow these instructions to install it.




2.     Windows Defender:

Windows Defender might block or interfere with the installation because it treats new software as unknown until it gets used to it. If this happens, you can temporarily close Windows Defender, install the software, and then turn Defender back on.

Download Pro Geez IME ፕሮ ግእዝ ግቤትን ያውርዱ